OLF Army group killed over 186 Amhara civilians in the Ethiopian region of Oromia
OLF Army group Gunmen killed over 186 Amhara civilians in the Ethiopian region of Oromia. The number of Amhara killed last night by OLF in Babo Woreda, Welega Zone of Oromia State has reached 186. It may be higher.
A rebel group in Ethiopia’s restive Oromia region carried out a “terror attack” this week that killed over 186 Amhara ethnic civilians.
The attack took place in the western part of the Wollega area, where Ethiopian soldiers have been fighting an armed group known as the Oromo Liberation Army (OLA), the Oromia regional government said in a statement.
(አሚኮ) - በምዕራብ ወለጋ ባቦ ገንቤል ወረዳ በቂ የሆነ የጸጥታ ኃይል ባለመሰማራቱ በአካባቢው ውጥረት መኖሩን ከጥቃቱ የተረፉ አማራዎች ገለጹ፡፡በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ አካባቢ በተፈጸመው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በርካታ አማራዎች ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ይህን ዘገባ እስከምናጠናቅርበት ጊዜ ድረስም የቀብር ሥነ ሥርዓት እየተፈፀመ እንደነበር ከጥቃቱ የተረፉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ከተፈፀመው ጭፍጨፋ በኋላ በአካባቢው ውጥረት ነግሶ እንዳደረ የነገሩን አስተያየት ሰጭዎቹ የአካባቢው ማኅበረሰብ በአንድ አካባቢ ተሰባስቦ በስጋት ሌሊቱን አሳልፏል ነው ያሉት፡፡
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኀይል በአካባቢው ቢኖርም ቁጥራቸው ውስን በመሆኑ የሕዝቡን ስጋት የሚቀርፉ አይደሉም ነው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፡፡በአካባቢው የሽብርተኛው ቡድን ሙሉ በሙሉ እስካልፀዳ ድረስ ስጋቱ በዘላቂነት ሊቀረፍ እንደማይችልም ነው የተናገሩት፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት የሰጠው መግለጫ አሳዝኖናል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ የሟቾች ቁጥር በተዛባ መልኩ ከመቅረቡ ባለፈ ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባ አማራዎች ሆነው ሳለ ነገሩን ለማድበስበስ የተሄደበት መንገድ ከዚህ በኋላም መፍትሄ እንደማይኖረው አመላካች ነው ብለዋል፡፡
በኦነግ ሸኔ ላይ ተወሰደ የሚባለው እርምጃም በአካባቢው ማኅበረሰብ ዓይን ያልታየ እና ማስተባበያ ነው ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም ግድያ በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የተረፉ ዜጎች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል ያሉት አስተያየት ሰጭዎች ከደረሰባቸው ስብራት አገግመው በቀጣይ ህይዎታቸው ዙሪያ መወሰን እስኪችሉ ድረስ በቂ የጸጥታ ኀይል ወደ አካባቢው እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡